NutriOpia is a diet and nutrition consultancy center that focuses on helping people with personalized nutrition plans, tailored to their individual needs and preferences. It was established in December 2021 by two visionary dietitians as part of ZEMAKEL Trading PLC.

nutriopia ኮሌስትሮልን ለመቀነስ እንዴት እንመገብ ?

ኮሌስትሮልን በቀላሉ ለመረዳት በደም / በደም ስሮች ውስጥ የሚገኝ ቅባት ነው ልንል እንችላለን። ይህም ከደም ስር እና ልብ ጤና ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አለው። ኮሌስትሮል በአብዛኛው በሰውነታችን ውስጥ በተለይ በጉበት ውስጥ የሚመረት ሲሆን አነስተኛ መጠን ደግሞ ከምንመገበው ምግብ (በተለይ ከእንስሣት ተዋጽዖዎች) ጋር ተያይዞ በሰውነታችን ውስጥ ይገኛል ፤ ይህም ቢሆን ግን አመጋገባችንን በመቆጣጠር በሰውነታችን ውስጥ ሊገኝ የሚችል አላስፈላጊ ኮሌስትሮልን ልንቆጣጠረው እንችላለን።

ኮሌስትሮልን ለመቀነስ እንዴት እንመገብ ?

በቅድሚያ ስለኮሌስትሮል ምንነት ጥቂት ማለት ይጠቅማል። ኮሌስትሮልን በቀላሉ ለመረዳት በደም / በደም ስሮች ውስጥ የሚገኝ ቅባት ነው ልንል እንችላለን። ይህም ከደም ስር እና ልብ ጤና ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አለው። ኮሌስትሮል በአብዛኛው በሰውነታችን ውስጥ በተለይ በጉበት ውስጥ የሚመረት ሲሆን አነስተኛ መጠን ደግሞ ከምንመገበው ምግብ (በተለይ ከእንስሣት ተዋጽዖዎች) ጋር ተያይዞ በሰውነታችን ውስጥ ይገኛል ፤ ይህም ቢሆን ግን አመጋገባችንን በመቆጣጠር በሰውነታችን ውስጥ ሊገኝ የሚችል አላስፈላጊ ኮሌስትሮልን ልንቆጣጠረው እንችላለን።

ኮሌስትሮል በሁለት አይነት ሁኔታ በሰውነታችን ውስጥ ሊገኝ ይችላል፤ ይህም ጥሩ ኮሌስትሮል (Good cholesterol) እና መጥፎ ኮሌስትሮል (Bad cholesterol) በመባል የሚገለጽ ነው።

በሕክምና ወቅት ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ስናስብ እንድንቀንስ የሚፈለገው መጥፎውን ኮሌስትሮል (LDL) ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ጥሩ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት (HDL) መጨመር እንፈልጋለን።

አመጋገባችንን ውስጥ ምን ብናካትት መጥፎ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት መቀነስ እንችላለን?

እንደ አጠቃላይ አመጋገባችን አትክልት እና ፍራፍሬ ተዋጽዖዎች እና ጤናማ ቅባቶች ላይ ዋነኛ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል። ስለዚህ እለት እለት በእያንዳንዱ ምግባችን ውስጥ በቂ አትክልት ማካተት እና በቀን ውስጥ በቂ ፍራፍሬ መመገባችንን እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል። በተጨማሪም በልዩ ትኩረት እነዚህን የምግብ አይነቶች ብንዘወትር ይጠቅማል።

1.       ያልተፈተጉ እህሎች በተለይ

2.      ጥራጥሬዎች (ድፍን ምስር፣ ባቄላ፣ አተር፣ ቦሎቄ ወዘተ)

3.      አትክልቶች በተለይ ደበርጃን (Egg plant) እና ሚያ (Okra)

4.      የቅባት እህሎች (ተልባ፣ ለውዝ እና የለውዝ ዝርያዎች

5.      ፍራፍሬዎች (ፖም፣ እንጆሪ፣ ወይን፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና ተመሳሳይ ዝርያዎች)

6.      የወይራ ዘይት

በተቃራኒው ማስወገድ ያለብን የምግብ አይነቶች ደግሞ

1.       በጥልቅ ዘይት / ቅባት የተጠበሱ ምግቦች

2.      ከፍተኛ የስብ መጠን / ጮማ

3.      ከፍተኛ የጨው መጠን

4.      በፋብሪካ የተቀነባበሩ እና የታሸጉ ምግቦች

5.      ስኳር እና ልዩ ልዪ ተፈጠሮአዊ ያልሆኑ ማጣፈጫዎች ናቸው።

በተጨማሪም

·       ጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

·       ልከኛ የሰውነት ክብደት እና የሰውነት ስብ መጠን መያዝ

·       እንዲሁም የአልኮል መጠጥ እና ሲጋራን ማስወገድ

ይህን የጤና እክል ለመከላከልም ሆነ ለመቆጣጠር ይረዳል።

መልካም እና ጤናማ ጊዜን ተመኘን!

ኑትሪዮጵያ!

 

Image