ኤሌክትሮላይቶች በደም፣ በህብረ ሕዋሳት እና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚገኙ ማዕድናት ናቸው፡፡ በሰውነት ውስጥ የፈሳሽና ማዕድናት መጠን ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋሉ (ይህም ሁለት ሶስተኛው በህዋሳት ውስጥ እንዲሁም አንድ ሶስተኛው ደግሞ ከህዋሳት ውጪ ይሆናል፡፡)
ምንድን ናቸው?
ኤሌክትሮላይቶች በደም፣ በህብረ ሕዋሳት እና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚገኙ ማዕድናት ናቸው፡፡
ጥቅማቸው?
በሰውነት ውስጥ የፈሳሽና ማዕድናት መጠን ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋሉ (ይህም ሁለት ሶስተኛው በህዋሳት ውስጥ እንዲሁም አንድ ሶስተኛው ደግሞ ከህዋሳት ውጪ ይሆናል፡፡)
ለምን?
ከመጠን ያለፈ ውሃ በህዋሳት የውስጥ ክፍል የሚጠራቀም ከሆነ ሴሎች ሊፈነዱ ይችላሉ፤ እንዲሁም በርካታ የውሃ መጠን ህዋሳትን ከለቀቀ ህዋሳት ቅርጻቸውን በማጣት ፈሳሽ የመያዝ አቅማቸው ይጠፋል፡፡ ከመጠን ያለፈ የፈሳሽ እና ማዕድናት ከሰውነት መውጣት ይህንን ሚዛን ያዛባዋል፡፡ በመደበኛው ሁኔታ ሰውነታችን በተቻለ ይህንን የሚዛንን መዛባት በራሱ ለማስተካከል ይሞክራል፤ ነገር ግን አንዳንድ ሁኔታዎች እና መድሃኒቶች ከአቅም በላይ ሊያደርጉበት ይችላሉ፡፡
እንዴት?
የቆየ እና ከበድ ያለ ማስመለስ እና ማስቀመጥ፣ ከባድ የሰውነት ላብ፣ ቃጠሎ እና የአደጋ ቁስሎች ሰውነት ያለምንም እገዛ የፈሽና የማእድናት ሚዛኑን ለመጠበቅ ሊያዳግቱት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም ሰውነት የፈሳሽና ማዕድናትን ሚዛን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሰውነት ፈሳሾችን የአሲድነት መጠንም ለመቆጣጠር ይጠቀምባቸዋል፡፡ በየትኛውም አቅጣጫ ያለ የልክ መዛባት የሰውነትን ገንቢ ንጥረ ነገሮች በማበላሸት ጤናማውን የሰውነት ተግባር ሊያዛባ ይችላል፡፡
ሌሎች ጥቅሞችስ?
በተጨማሪም ኤሌክትሮላይቶች ንጥረ ነገሮች ወደ ህዋሳት እንዲገቡ፣ የሰውነት ውጋጆች በሚገባ እንዲወጡ፣ ነርቮች መልእክትን በሚገባ እንዲያስተላልፉ እንዲሁም አንጎልና ልብ ተግባራቸውን በሚገባ እንዲወጡ ይረዳሉ፡፡
የኤሌክትሮላይቶች ሚዛን መዛባት ምንን ሊጎዳ ይችላል?
ስሜትን የመቆጣጠር፣ የአተነፋፈስ፣ የልብ ምት፣ የሰውነት አቅም፣ የአንጎል ስራን በአግባብ የማከናወን እና የመሳሰሉትን
የኤሌክትሮላይቶች ሚዛን መዛባት ዋና ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
በተለያዩ ህመሞች ወይም የሰውነትን ክብደት በፍጥነት ለመቀነስ በሚል በሚወሰዱ የተለያዩ መድሃኒቶች አማካኝነት በሚከሰት ከባድ ማስመለስ እና ማስቀመጥ
ምግብንና ፈሳሽን በሚገባ መጠን ባለመውሰድ
ከልክ ባለፈ የሰውነት ላብ
በተለያዩ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት (የካንሰር ሕክምናን ጨምሮ)
የአመጋገብ የጤና እክሎች
የጉበት፣ የኩላሊት እና የልብ የጤና ችግሮች ወ.ዘ.ተ
ምን ማድረግ አለብኝ?
የጤና ባለሙያዎችን ያግኙ፤ ይህ የጤና እክል ገጥሞት እንደሆነ ያረጋግጡ ከዚያም ከሚመለከታቸው ልዩ ልዩ የጤና ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር በህክምናው ላይ አብረው ይስሩ፡፡